ትዝል ይሆናል። በድንገት የምትሠራው ትርጉም ሊያጣብህ ወይም ሊምታታብህ ይችላል። ካላሰብከው አቅጣጫ የመጣ ርኅራኄ አልባ ትችት በድንዛዜ ይመታህም ይሆናል። በዚህ ጊዜ ቆም ብለህ ብድራትህን ተመልከት። የሚጠብቅህን ክብር አስታውስ። “ለተጠማ ጎረቤቱ አንድ ጽዋ ቀዝቃዛ ውኃ የሚሰጥ ሰው ሽልማቱ የማይጎድል ከሆነ የዘላለምን ሕይወት ምንጭ ማፍለቅ የሚችሉ ማለፊያ መጻሕፍትን በጎረቤቶቹ እጅ ላይ የሚያኖር ሰው ሽልማት ምንኛ የላቀ ይሆን?” የሚለው የቶማስ ኤ ኬምፐስ አባባል ያንቃህ። ወይም “አንድ መጽሐፍ ለአንባቢህ ስታቀርብለት
የምትሰጠው ቀለም፣ ወረቀትና ሙጫ
አይደለም፤ አዲስ መረዳትን እንጂ
” ያለው የማላስታውሰው ግለሰብ ትዝ
ይበልህና ሐሞትህን አኮስትር።
ስለ
አንድ ነገር ግን እጅግ
ተጠንቀቅ። ዋሽንግተን ዲ.ሲ
እንብርት ላይ ያለውን ብሔራዊ "የአየርና ጠፈር ሙዚየም" ስጎበኝ “ብዙዎችን ለሥራ የሚያነቃቃ ፍላጎት የትኛው ነው?” ሲል ጠየቀ አስጎብኚው። ምላሹም ገንዘብ ነበር። እኔና አንተን ግን ለሥራ የሚያነሣሣን መንፈስ ቅዱስ ነው። ገንዘብ ባሪያችን እንጂ ጌታችን አይደለም። መጽሐፍ ሸጠህ ለመክበር የምታስብ ከሆነ ሌላ የተባረከ ንግድ ክፈት። መብትህ ነው። መጽሐፎቹን ሸጠህ ግን ለሚቀጥለው ማሳተሚያ ካገኘህ ያ ይበቃሃል።
በቤሪያ የስልክ መስመሮች ላይ ነዘጠኝ ሳምንት ከሰጠሁት ትምህርት የተቀነጨበ
No comments:
Post a Comment