ከሦስት ሳምንታት በፊት በጆርጅያ አንድ የሕዝብ
ት/ቤት ውስጥ የተካሄደው የጥምቀት ሥርዓትና “እግዚአብሔር
አሁንም በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ በሥራ ላይ ነው” በሚል መሪ ዐረፍተ ነገር ዩቱብ ላይ የተለቀቀው ይህንኑ የሚያሳይ ቪዲዮ ውዝግብ አስነሥቷል። ቪዲዮው የተከላካዮች አሠልጣኝና የስፖርት
መምህሩን ጨምሮ 18 የቪላ ሪካ እግር ኳስ ቡድን ተጫዋቾች በየተራ ሲጠመቁ ያሳያል።
የዕብራውያን ጸሓፊ ይህንኑ ሲያስረግጥ እንዲህ ይለናል። “ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፥ የእሳትን ኃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፥ ከድካማቸው በረቱ፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ። ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ (ዕብ. 12፡ 34-38)።
ነፃነት ከኃይማኖት(Freedom from Religion)
የተሰኘ ድርጅት ፕሬዚዳንት የሆኑት ሎሪ ጌይለር "ልጆቻችን እንድትጫወቱ ጸልዩ ተብለው ሊገደዱ አይገባም። ይህ ማስፈራራትና እምነትን ማስካድ ነው" ሲሉ ድርጊቱን ተቃውመዋል። ለት/ ቤቱ በጻፉት ደብዳቤም "አስቸኳይ
ምርመራ አድርጎ እርምጃ እንዲወስድና ከዚህም በኋላ ይህ ዓይነቱ ሕገወጥ ሃይማኖታዊ ልምምድ እንዲቆም እንጠይቃለን” ሲሉ
አሳስበዋል”። በነገራችን ላይ ይህ ድርጅት ቀደም
ብሎም እዚያው ጆርጂያ ያለ ሌላ ት/ ቤትን ከሦ እንደነበር ይታወሳል። “ይጸልያሉ” ብሎ!
በኬንታኪ ደግሞ ግብረሰዶማዊ ጋብቻ የመጀመሪያውን ሠርቲፊኬት
የተቀበሉት ዊልያም ስሚዝና ጄምስ ዬትስ ገና ፈንድቀው አላባሩም። ስድስት ዓመታት ሙሉ የደከሙለት ዐመፅ ጊዜያዊ ድል
አግኝቶአልና።ተጋቢዎቹ ገና
ፍርድ ቤቱ ከመከፈቱ በሁለት ሰዓት እዚያ የተገኘኡ ሲሆን ደጋፊዎቻቸውም “ፍቅር ያሸንፋል” እያሉ ይጮኹ ነበር። ድንቄም!
ይህንን አልፈቅድም ብላ የተቃወመችው ኪም ዴቪስ የት ናት? እሥር ቤት!
ምን በደለች?
የአዳምና ሔዋንን እንጂ የአዳምና ብሩስን ጋብቻ አልቀበልም ብላ!
የእምነት ነፃነት ተምሳሌት በምትባለው አሜሪካም ጭምር አንድ እውነት እየበራልን ነው። በርግጥ ክርስቶስን እየመሰሉ
ለመኖር የሚወድዱ ይሰደዳሉ። ያፈጠጠና የተረሳ እውነት ይኸው! ሰማያዊው ሩጫ መከራ አለበት። አዎን ጭብጨባና ፉጨት ላያጅበን ይችላል። እንዲያውም ተቃውሞና ስደት
ሊያባርረን መቻሉ ግልጽ ነው። በየመንገዱ የሚቀመስ ውኃ በማቀበል ፈንታ ገዝተን የጨበጥነውን እንኳ ከእጃችን የሚያራግፉ
የዲያብሎስ ጎረምሳ ልጆች ያገኙን ይሆናል። ከፊትና ኋላችን የሚንጋጋው ተሽከርካሪ የመጀመሪያ እርዳታ ሰጭ መሆኑ ቀርቶ ሊገጨን
የተላከ የሞት መልእክተኛ ሊሆንም ይችላል። እናም ሰማያዊው ሩጫ ከምድራዊው በመከራ ይለያል።የቀደሙት ቅዱሳንም ሩጫቸውን የጨረሱት በብዙ አበሳ ነው።
ከቤተሰባቸው ጀምሮ አሳዳጃቸው ብዙ ነበር። መንግሥታት መከራቸውን አብልተዋቸዋል። ከአንበሳ ጋር እንዲታገሉ በተራበ አውሬ
እንዲበሉ አድርገዋቸዋል።የዕብራውያን ጸሓፊ ይህንኑ ሲያስረግጥ እንዲህ ይለናል። “ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፥ የእሳትን ኃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፥ ከድካማቸው በረቱ፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ። ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ (ዕብ. 12፡ 34-38)።
አልሰማሁም እንዳትል.....አልሰማሁም እንዳትይ....
በተመሳሳይ አሳብ ላይ ለመናገር ከቤቴ ከመውጣቴ በፊት ....