ጸሐፊ አንድ መሠረታዊ ፍላጎት አለው። እርሱም መነበብ ይባላል። ሌሎቹ ከዚያ የሚከተሉ ናቸው። እኔም ያዘጋጀኋቸውን መጻሕፍት መደርደሪያ ላይ እንዲቀመጡ ሳይሆን እንዲነበቡ በዓለም ዙሪያ ለመበተን ሳልም ብዙ ዓመታትን ፈጅቶብኛል።
ለሁሉም ጊዜ አለው ሲል ጠቢቡ ሰለሞን ተናግሯል። ልክ ነው። እኔም በመጨረሻው ተሳካልኝ መሰለኝ። ለጠቅላላ እውቀት የሚበጁና ለነፍስ ዕውቀት የሚጠቅሙ ጽሑፎችን በድረገጽ ለማሰራጨት ሳስብ በርካታ ዓመታት አልፈው ነበርና። ከበፊቱም መፃፍ እንጂ ኮምፒውተር ላይ መጠበብ ብዙም አይስበኝም። ለድርሰት ሥራዎቼም ወደመቀምራዊ ሳይንስ የዘለቅሁት ወድጄ አይደለም። በተያቢዎች ተማርሬ ነው። ከዚያ ውጭ ብዙም አልራቀቅበትም። ምናልባት ስላልተሰጠኝ ይሆን? ግን ያ ታሪክ ሆነ። አሁን ጊዜው በአየር ላይ መንሳፈፊያ ነው። ባለዌብሳይት ሆኜላችኋለሁ።http://www.alemayehu.org/ ይላል መጠሪያው። ለማስታወስም ብዙ አይቸግር። ይህን ድረ ገጽ የከፈትነው እስካሁን የተዘጋጁትና ወደፊትም የሚሰናዱት መጻሕፍት፣ ጽሑፎችና በራሪ ወረቀቶች በየትኛውም ሥፍራና በማንኛውም ሰዓት በነፃ ይነበቡ ዘንድ ነው። አዎን እዚህ ያኖርናቸው ወደፊትም የምናኖራቸው የጽሑፍ ውጤቶች በሙሉ ጭኖ ለማንበብም ይሁን አባዝቶ ያለክፍያ ለማደል ነፃ ናቸው። በነፃ የተቀበሉትን በነፃ መስጠት የሚለውስ ይህንኑ አይደል? ድጋፍ የተቀበልነውም ይሁን የምንቀበለው የፍቅር ስጦታ ለማበርከት በራሳቸው ከተነሣሡ ወገኖች ብቻ ነው። ይህ የጸና አቋማችን ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል። ገንዘብ ሊገዛው የማይችል ጸሎት የተሰኘ ውድ ስጦታን ግን ያለማመንታት እንቀበላለን። በተለይ ወደአብ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚጸልዩ ሰዎች ምልጃ እዚህ አድርሶናልና መቼም በቃን አንልም። እነሆ ጽሑፎቹን ተጠቀሙባቸው። ሌሎችንም ወደዚሁ ጋብዟቸው። መልካም ንባብ!
ለብዙዎች በረከት እየሆነ ነው። በሁለት ሳምንት ዕድሜው የምኖርባትን አሜሪካ እና የትውልድ አገሬን ኢትዮጵያ ጨምሮ በ22 አገሮች በሚኖሩ አንባብያን ተጎብኝቷል። እነርሱም ካናዳ፣ ሊባኖስ፣ ጀርመን፣ ኖርዌይ፣ ሆላንድ፣ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ስዊድን፣ አውስትራሊያ፣ ኦስትሪያ፣ ባሕሬይን፣ ፊንላንድ፣ ኢጣሊያ፣ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች፣ ሕንድ፣ አየርላንድ፣ እስራኤል፣ ፊሊፒንስ፣ ሳዑዲ ዐረቢያና እንግሊዝ ናቸው። በአዲስ አበባ፣ ላንካስተር፣ ላስቬጋስ፣ ጌተስበርግ፣ ኢንዲያና፣ ቦልቲሞር፣ ሳንሆዜ፣ ኖርዝ ካሮላይና፣ ሚኒሦታ ቦስተንና ፊላደልፍያ ከነበሩን የጸሎት አጋሮች በተጨማሪ አሁን በዚህ ክንውን ከዓለም ዙሪያ ከባሕሬይን፣ ጀርመን፣ ሊባኖስ፣ ሳዑዲ ዐረቢያና ፊንላንድ ከአሜሪካ ክፍለ ግዛቶች ደግሞ ከቨርጂኒያ፣ ሒውስተን፣ አሪዞናና ፍሎሪዳ ተጨምረውልናል።
ይህንኑ ለማገዝ የከፈትኩት አዲሱ የፌስቡክ ገጼም https://www.facebook.com/Alemayehu-Mammo-1717792215150677/ ተቀባይነቱ እየሰፋ ነው። በጥቅሉ የአቅጣጫ ቅያሬው እጅግ አበረታች ውጤት እየተገኘበት ነውና ደስ ተሰኝቼበታለሁ። በፌስቡክ ወዳጅነት የዘለቃችሁ የተለያዩ ጽሑፎችና አስተያየቶችን በመውደድ (LIKE) ፣ በማዳረስ (SHARE)እና የተሰማችሁን በመጻፍ ከጎኔ የቆማችሁትን ሁሉ ለማመስገን እወዳለሁ። አሁንም ድረገጹን ሌሎች እንዲጠቀሙበት ከማበረታታት አትቦዝኑ። አዲሱ የፌስቡክ ገጼንም ወደድኩት (LIKE) የሚለውን በመጫን ቀጣዮቹን ሥራዎች ተከታተሉ። ሌሎች ወዳጆቻችሁም ይህንኑ እንዲያደርጉ አስታውሷቸው። በመጨረሻም ምሳሌአዊ ንግግሮችን ለማንበብ በሚከተለው አድራሻዬ ትዊተር ላይ ተከተሉኝ።https://twitter.com/AlemayehuMammo1

No comments:
Post a Comment