Saturday, February 14, 2015

ራስህን አድን!


"ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፣ በእነዚህም ጽና፣ ይህን ብታደርግ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና" የሚለውና 1 ጢሞ. 416 ላይ የተመሠረተው የፊኒ ስብከት እንደሚከተለው ነው። አነሣሴ ሰባኪዎችን ለመስበክ አይደለም። ይልቁንስ በመነሻ ንባቡ ላይ ቃል የተገባውን ደኅንነት በእርግጠኝነት ይጨብጡት ዘንድ አንዳንድ ነጥቦችን ለማመላከት ነውበማለት የጀመረው ታላቁ ወንጌላዊ ቻርልስ ፊኒ መልእክቱን በተራ ቁጥሮች በመደርደር እንዲህ አስቀምጧቸዋል።
1)              ወንጌልን የምትሰብከው ልክ እንደ ክርስቶስ ፍቅር ግድ ብሎህ እንደሆነ እርግጠኛ ሁን።
2)              ኃይል እንደወረደብህ በመንፈስ ቅዱስም እንደተጠመቅህ አረጋግጥ። 
3)              ወንጌልን መስበክ ወደአእምሮህ ሽው ያለ አሳብ ሳይሆን ውስጥህን የሞላ ነገር መሆኑን እርግጠኛ ሁን። ይህንን ስል የሌሎች መዳን ልብህን የሞላ በጽኑ ሞኞትም የተደገፈ ይሁን ማለቴ ነው። ልብህ ያላረፈበትን አታድርግ።
4)              ከእግዚአብሔር ጋር ተጣብቀህ መራመድን አታቋርጥ።
5)              መጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር አንድ መጽሐፍህ ይሁን። መለኮታዊውን ብርሃን እየተጠባበቅህ ተንበርክከህና አብዝተህ አጥናው።
6)            ማብራሪያዎችን ስታጠና ተጠንቀቅ። እንደአመቺነቱ አንብባቸው። ግን የራስህን ሚዛህ በመንፈስ ቅዱስ ብርሃን ጠብቅ።
7)              ስትናገርም ይሁን ስትሠራ ፍቃድህን፤ አሳብና ድርጊትህን በንጽሕና ጠብቅ።
8)              ይድኑ ዘንድ ያለህ ፍላጎት እንዲበረታ ኃጢአተኞች የሚጋፈጡት አደጋና ፀፀት ከአሳብህ አይጥፋ።
9)              ደግሞም ክርስቶስ ለኃጢአተኞች ያለውን ገደብ የለሽ ርኅራኄና ፍቅር አሰላስል።
10)           ስለዚህ አንተም ልትሞትላቸው እስከመፍቀድ ድረስ ውደዳቸው።
11)           መላ አስተሳሰብህን ሰዎችን እንዴት ማዳን እንደምትችል ለማሰላሰል አውለው።  ትልቁና የምታተኩርበት የጥናትህ ክፍልም ይሄ ይሁን።
12)           ከጽኑ መሻትህ ሊጎትትህ ከሚሞክር ማንኛውም ፈተና ራስህን ጠብቅ። ከዚህ ተልዕኮ አሳብህ እንዲነሣ ከቶም አትፍቀድ።
13)           ለዚህ ሥራ በሚያስፈልግህ ሁሉ ይረዳህ ዘንድ ክርስቶስ ሁልጊዜና በሁሉም ሥፍራ አብሮህ እንዳለ ጽኑ እምነት ይኑርህ።
14)           ነፍሶችንም የሚሰበስብ እርሱ ጠቢብ ነው (ምሳ.11:30) ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል(ያዕ.1:5) ተብሎ ተጽፎአል ስለሆነም ይህን አስታውስ። ነፍሳትን ለክርስቶስ ማሸነፍ የሚያስችል ጥበብ ይኑርህ።
15)           በእግዚአብሔር ለሥራው ከተጠራህ ርሱ ጋር የምትሟገተው ለስኬታማነት የሚያስፈልግህን ሁሉ ታገኝ ዘንድ ይሁን።

16)           በጊዜውም ያለጊዜውም (2 ጢሞ.4:2) ጠንቃቃና ትጉ ሁን። 
ይቀጥላል.....

No comments:

Post a Comment