በሥርዓት መኖር በዘመናችን የማይወደድ ቃል ሆኗል። ይሄ ሲነሣበት አትንኩኝ ባዩ መብዛቱ እውን ነው። የዚህ ዓይነቱ ሰው እንቁላል ለመሰብሰብ በተነሳው ዶሮ አርቢ ይመስላል። ወደ ዶሮዎች ቤት ሲሄድ ሳለ
የውሃ መሳቢያው እንደሚያንጠባጥብ አየ። ቆም ብሎ ሊጠግነው ሞከረ። ግን ሌላ መቀየሪያ እንደሚያስፈልገው በተረዳ ጊዜ ያንን ለማምጣት
ወደመጋዘኑ ሄደ። በመንገዱ ላይ ካሉ ክምሮች የተንጋደደ ስላጋጠመው ለዚያ የሚረዳው መሳሪያ ይፈልግ ገባ። በዚያ ደግሞ እጀታው የተሰበረ
መጥረጊያ ስለገጠመው «ማስታወሻ መጻፍና ወደ ከተማ ስወጣ ሌላ መግዛት ይኖርብኛል» ሲል ከራሱ ጋር ተማከረ።
በዚህ አካሔድ ዶሮ አርቢው እንቁላል መሰብሰብም ሆነ ሌላ ሥራ
ማከናወን እንደማይችል ግልጽ ነው። ሊገለጽ በማይችል አኳኋን ደግሞም ሊመካባት በሚችል ዘይቤ ይህ ሰው በሥራ ተወጥሯል። ትንፋሽ ግን የለውም። ስለሆነም ይህ ስው ወደደም ጠላ ሊለቅቀው ከማይችል
የራሱ ትጋት ጋር ተቆራኝቷል። ከዚህ ነጻ ለመውጣት አንዱና ብቸኛው መንገድ ራስን በሥርዓት መምራት ነው። ሥነ-ሥርዓት።»
ቅድስናን መፈለግ ከሚለው አዛማጅ ትርጉም መጽሓፌ የተወሰደ
No comments:
Post a Comment