ፕሬዚዳንት ፍሪንክሊን ዲ - ሩዝቬልት ጥር 3/1941 ዓ.ም. ለምክር ቤታቸው ንግግር አድርገው ነበር፡፡ ከጦርነቱ በኋላ ሰለሚመኙት ዓለም ራዕያቸውን ሲያካፍሉ ሰዎች ሁሉ ሊለማመዷቸውና ሐሤት ሊያደርጉባቸው ስለሚገቡት አራት መሠረታዊ ነፃነቶች አወሱ፡፡ እነርሱም የንግግር ነፃነት፣ የአምልኮ ነፃነት፣ የመሠረታዊ ፍላጎት ነፃነትና ከፍርሀት ነፃ መሆን ናቸው፡፡
በእርግጥ እነዚህ ነፃነቶች በዚያ ዘመን ከነበሩበት ሁኔታ ይልቅ አሁን በተሻለና በላቀ ደረጃ ተግባራዊ ሆነዋል፡፡ ዓላማችን ግን ሌላ አምስተኛ ነፃነት ትሻለች፡፡ ሰው ከኃጢአት ተፈጥሮው ነፃ መሆን ያስፈልገዋልና፡፡
No comments:
Post a Comment