“ከሁሉ በላይ ፈቃዳቸውን ማሸነፍና
እንዲታዘዙ ማስተማር ነበረብኝ። ለምንና እንዴት የሚለው እንዲገባቸው ማድረግ የጊዜ ጉዳይ ነው። በመስማት
ችሎታቸው ልክ በዝግታ መማር ይኖርባቸዋል። ነገር ግን
መታዘዝን መማራቸው ወሳኝ ነው። ያን ቶሎ መማራቸው እጅግ
አንገብጋቢ ነው።”
“አዎን
የልጆችን አመለካከት በቅጡ ለመቅረፅ ዋናው ጉዳይ አስቀድሞ ፈቃዳቸውን ማሸነፍና እንዲታዘዙ ማለማመድ ነው። ግን ደግሜ ልበለውና እስኪገባቸው ጊዜ ይወስዳል፤ እናም
እስኪለምዱት ድረስ ቀስ በቀስ ሊከናወን ይገባዋል። ፈቃዳቸውን
ማሸነፍ ለነገ የሚባል ጉዳይ ሳይሆን በተቻለ መጠን ፈጥኖ ሊከወን የሚገባው ወሳኝ ተግባር ነው። ለምን ከተባለ በጊዜ ተግሣጽ ካላገኙ በቀር ግትሮችና ጠማሞች ስለሚሆኑ ያን ለማስወገድ
ይቸግራል። ኋላ የግድ መስተካከል ያለበት የዐመል ችግር ልጆቻቸው ላይ እያዩ ቸል የሚሉ ወላጆችን
ጨካኝ ነው የምላቸው። አንዳንዶቹም ልክ እንደስፖርት ሥርዓትን
ለልጆች በኋላ ማስተማር ይቻላል ብለው የሚያምኑ ደካሞች ናቸው።”
“ የወደፊት
ኑሮአቸውን አመላካች ነውና ይህን ጉዳይ እንደዋዛ አንሥቼ ላልፈው አልፈልግም። ፈቃድ ለኃጢአትም ይሁን መከራ በር ከፋች
ነው። እምነትም እኮ ቢሆን የራሳችንን ሳይሆን የእግዚብሔርን ፈቃድ ማድረግ ነው። ልጆችን
ወደፍጹም ፈቃድ ለማምጣት ስንተጋ መፍቀዳችን ውጤት አልባ
መከልከላችንም ያለፍሬ ሊሆን አይችልም። መንግሥተ ሰማይና ሲዖልም የፍቃድ ውጤቶች ናቸው። እናም የልጆቹን ፈቃድ ለማስገዛት
የሚሠራ ሰው የእግዚአብሔር አጋር ነው። ነፍስን ለማደስና ለማዳን ይሠራልና። በአንፃሩ የልጆቹን ፈቃድ መረን የሚለቅቀው ሰው ከዲያብሎስ ጋር ወግኗል።
በልጆቹ ዐይን ፊት እምነትን የማይጨበጥ መዳንንም የማይሞከር ያደርገዋል። ሳይታወቀው ልጆቹ በነፍስና በሥጋ የጠፉ እንዲሆኑ
እየተጋ ነው።”
ሱዛና ዌስሊ ለልጇ ጆን ከጻፈችው ደብዳቤ
No comments:
Post a Comment