በክፍል አንድ ከአንድ እስከአስራስድስት በክፍል ሁለት ከ17-32
በክፍል ሦስት ደግሞ ከ33-47 አስፍረናል።
እነዚህ
ከ48-64
ያሉት ናቸው።
49 ለሌሎች ሰብከህ ራስህ የተጣልህ እንዳትሆን ሥጋህን ጎስም (1 ቆሮ. 9:27)።
50 ለእግዚአብሔር እንደሚጠየቅ ሰው ሆነህ ነፍሳትን ፈልግ።
51 ለመዳን የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ለሰሚዎችህ ታስተምር ዘንድ ትጉ ተማሪ ሁን።
52 በሃብታሞች አትደለል።
53 የድሆችን ፍላጎት ለማወቅና እነርሱን ለማስተማር የተለየ ትኩረት አድርግ።
54 ለኃጢአት እንድታመቻምች የሚያደርግህ ከሆነ በለጋሾች አትደለል።
55 አብላጫ ቁጥር ባላቸው አድማጮችህ ፊት ከበሬታን ይነፍግሃልና በአደባባይ ለማኝ መስለህ አትታይ።
56 ልቅ፤ ስሕተትና ጎጂ የሆነ ነገር ላለመናገር ይልቁንም አፍህን ለመዝጋት ትልቅ ጥንቃቄ አድርግ።
57 በጎ ሕሊናህን እንዳታጣ፤ ቅዱሱን መንፈስ እንዳታሳዝን፤ ሕዝብህም ባንተ ላይ ያለውን አመኔታ እንዳታጣና የእግዚአብሔር ሞገስ እንዳይርቅህ የመጋቢነት አገልግሎትህን እውነተኛና ነፃ አድርግ።
58 ለመንጋው ምሳሌ ሁን። ስብከትህ በኑሮህ ይገለጥ። መንፈስህና ድርጊትህ የበለጠ አስተማሪ መሆናቸውን አስታውስ።
59 ሰዎች እግዚአብሔርና ጎረቤታቸውን በፍቅር ሊያገለግሉ ይገባል ብለህ ከሰበክህ አንተም ያንኑ አድርግ። ለደሞዝ ብቻ የምትሠራ የሚያስመስልህን አካሄድ ከአንተ አስወግድ።
60 ሕዝብህን በፍቅር አገለግል። እነርሱም በተራቸው ስለ አገልግሎትህ ገንዘብ ሳይሆን ፍቅርን እንዲክሱህ አበረታታቸው። ይህ ሁላችሁን ያነቃቃልና።
61 ዓለማዊ የሆኑ ጮሌዎችን ሊያነሣሣ አክሎም ንቀትን ሊያጭር ስለሚችል ለአንተና ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገንዘብ ሊለምን የተዘረጋ እጅህ ይሰብሰብ።
62 በተለይ ተባብሮ ነፍሳትን ለክርስቶስ ለመማረክ በሚመች ጊዜ ከሻይ ግብዣዎች፣ ለመስሕብ ብቻ ከሚደረጉ ገለጻዎችና እዚህም እዚያም ከሚደገሡ ጥሪዎች ራስህን አቅብ። የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት ስትጸልይና ስታቅድ አንዳንድ ከዓለማዊነት ያልራቁ አባሎችህ ለድግስ ይጋብዙህ ይሆናል፤ አትሂድ። እነርሱ ክበብ ውስጥ ከገባህ በጸሎትህ ሽንፈትን መከናነብህ አይቀርም። ክፉው ወደዚህ መሥመር ሊመራህ እንደሚሞክርም አትጠራጠር።
63 አትታለል። እንዲህ ዓይነቶቹን ግብዣዎች በእንዲህ ዓይነቱ ጊዜ በመቀበልህ ጉባዔው በመንፈሳዊ ሥልጣን ከፍ አያደርግህም። ስዎች ደስ ሊሰኙ ከወደዱና ወቅቱ ለግብዣ አመቺ ከሆነ ለሃይማኖታዊ ስብሰባም አመቺ መሆን አለበት። ተፅዕኖህ ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር ቤት ለመሳብ መዋል ሊውል ይገባል።
64 ክርስቶስን እወቀው። በየዕለቱም በእርሱ ኑር!
.
No comments:
Post a Comment