ክፍል ሁለት
ክፍል አንድ ከአንድ እስከአስራስድስት አስፍረናል። እነዚህ ከ17-32
ያሉት ናቸው።
1)
አሳባቸውን፣ ስሕተታቸውንና ፍላጎታቸውን ለመረዳት ትችል ዘንድ ስለመዳን ባላቸው ጥያቄ ላይ ከሁሉም ዓይነት አድማጮችህ ጋር አብዝተህ ተነጋገር። ትምህርትህን ከነርሱ ፍላጎት ጋር ለማዛመድ ትችል ዘንድ አመለካከታቸውንና ስሜታቸውን አጢን። ልማዶቻቸውን ልብ በል። ምን እንደተጋረደባቸውም አስተውል። ማወቅ የሚገባህን ሁሉ እወቅ።
2)
ሥራዬ ብለህ የምታደርጋቸው ሁሉ ትክክል መሆናቸውን አያያዝህም ርጋታ ያለተለየው መሆኑን አጢን። ከትንባሆ፤ የአልኮል መጠጥና አደንዛዥ ዕፆች ሌሎችም አንተን ሊያሳፍሩ ሌሎችንም ሊያሰናክሉ ከሚችሉ ነገሮች እድፍና ጠረን ነፃ መሆንህን ርግጠኛ ሁን።
3) ቁርጠኝነት አይጉደልህ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ እግዚአብሔርን አስቀድም (መዝ. 16:8)።
4) ለአንደበትህ ልጓም አብጅለት፤ ለከንቱና ዋጋ ቢስ ንግግር ራስህን አሳልፈህ አትስጥ።
5) መድረክ ላይ ስትወጣም ይሁን ከዚያ ስትወርድ ቁርጠኛና እርግጠኛ መሆንህን ሰዎች ይረዱት። ከእነርሱ ጋር ያለህ የዕለት ተዕለት ግንኙነት በሰንበት ቀን የምታቀርበውን ወሳኝ ትምህርት ዋጋ ቢስ አያድርገው።
6) ከተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ እንደማታውቅ ለሚቀርቡህ ሁሉ ይታወቅ። በክርስቶስ አምባሣደርነትህ ከእነርሱ ጋር ያለህ ሕብረት ስለነፍሳቸው መዳን ብቻ መሆኑን ይረዱት።
7) መሆን አለበት ብለህ የምታስተምረውን በምሳሌነት አሳይ። የምትሰብከውን ኑር።
8) ያልሆነ አሳብ ወይም ጥርጣሬ እንዳያስከትልና ንጽሕናህን እንዳይነካ በተለይ ከሴቶች ጋር ስለሚኖርህ ግንኙነት ተጠንቀቅ።
9) ደካማ ጎኖችህን ተከላከል። አላስፈላጊ ወደሆነ ነገርም ይሁን ርካሽ ፈንጠዝያ ፍለጋ ወደዚያ አቅጣጫ ከሚያዘሙህ አጋጣሚዎች ተጠንቀቅ።
10) በተፈጥሮህ ኮስታራ ወይም ገለልተኛ ከሆንክ መራራና ሰዎችን የማትቀርብ ሆነህ እንዳትቆጠር ተጠንቀቅ።
11) የሰውን ጆሮ ለማግኘት ብቻ የሚደረግን ጥረትና ካባ የለበሰ ውሸትን አስወግድ። ያኔ የማስመሰል ድርጊት ለመፈጸም አትፈተንም።
12) ጽናት፣ እውነተኝነትና ክርስቲያናዊ ባለቤትነት የሁለንተናዊ ኑሮህ መለያ ይሁኑ።
13) በቀንም ይሁን በማታ ሁልጊዜ ለጸሎትና ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ለማድረግ ብዙ ጊዜ ውሰድ። ይህም ለማዳን ብዙ ኃይል ይሆንልሃል። የዚህን ሕብረት መታጣት ግን የትኛውም ዓይነት ትምህርት ይሁን ጥናት ሊያካካሰው አይችልም። ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ከሌለህ እንደማንኛውም ሰው ደካማ ነህ።
14) ዳግም ልደት የለም የሚለውንና ያንንም ተከትሎ የነፍሳትን መዳን የሚጠራጠረውን ስሕተት አስወግድ።
15) ዳግም ልደት የሞራልና ይልቁንም የፍቃደኝነት ለውጥ መሆኑን ልብ በል።
16) ወንጌል የሰዎችን ልብ መለወጥ እንደሚችል ሆኖ ተዘጋጅቷል። ያንን በጥበብ ስትሰብከው ደግሞ ከመንፈስ ቅዱስ ውጤታማ እገዛ እንደምታገኝ ጠብቅ።
No comments:
Post a Comment