የምናነበው መጀመሪያ ለራሳችን ነው። ለራሳችን አንብበን ነው ቀጥሎ ለሌሎች የምንተርፈው። በአስራ ሰባት ዓመቴ ወደ መርከበኞች ትምህርት ቤት ገብቼ ነበር። ከተማርኳቸው የማይዘነጉ የእሳት ማጥፋት መመሪያዎች አንዱ “መጀመሪያ ራስህን ለማዳን በአግባቡ ልበስ፤ ከዚያ በኋላ ሌሎችን ከእሳቱ ለማውጣት ተንቀሳቀስ” ይላል። ነገርየው መንፈሳዊ አንድምታ እንዳለው የተረዳሁት ዘግይቼ ነው። አሁንም በምበርበት አውሮፕላን ሁሉ “የአየር እጥረት ከተፈጠረ ከጣሪያው የሚወርደውን ጭንብል ያጥልቁ፤ ከዚያ በኋላ ሌሎችን መርዳት ይችላሉ” ሲባል እሰማለሁ።
በእኔ አተያይ ይህ መርኅ ጥርት ብሎ የገባው ሰው ቢኖር ጳውሎስ ነው። ለመንፈሳዊ ልጁ ጢሞቴዎስ እንዲህ ብሎታልና። “ስትመጣ በጢሮአዳ ከአክርጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖሱንና መጻሕፍቱን ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ” 2 ጢሞ 4፡13። ይኸው አንባቢ ሰባኪ ነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ብዙዎቹን የጻፈ።
ሁለተኛው ታሪክን ለመቀየር ነው። ልጆቼ በሚማሩበት ትምህርት ቤት አንድ ነገር አስረግጠው ነግረዋቸዋል።አንባቢዎች መሪዎች ናቸው (ሪደርስ አር ሊደርስ) ብለው። አሁን ልጆቼና ንባብን ማለያየት የኔ ትልቁ ፈተና ሆኗል። መጽሐፍ ይዘው ከተቀመጡ ለምግብ እንኳ የምጠራቸው አንድም በልመና አልያም በቁጣ ነው። አሜሪካውያኑ የገባቸው አንድ እውነት ያለ ንባብ መጪውን ጊዜ መቀየር አይቻልም የሚል ሳይሆን አይቀርም ። በምርኮ ምድር የተደላደለውን ሕዝብ በቃህ ብሎ ወደገዛ መሬቱ የመለሰው ዳንኤል የዘመኑን ፍጻሜ ያስተዋለው የኤርምያስን መጽሐፍ በማንበብ ነበር (ዳን. 9:2)። በርግጥም ከጸሎት ቀጥሎ ለሰዎች የምንተርፍበት ትልቅ እሤት ንባብ ነው።
በመጨረሻም ከምንም ይልቅ ማንበባችን ጥበብን ፍለጋ ነው። እንደምናውቀው ጥበብ የምትገኘው በንባብ ብቻ አይደለም። በቅድሚያ ከባለቤቱ በመለመን ትገኛለች። ቃሉ “ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል” ይላልና (ያዕ. 1:5)።
ቀጥሎም በፈሪሃ እግዚአብሔር ትጨበጣለች። ይህንን የምሳሌ መጽሓፍ “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ” በማለት ያበራልናል (ምሳ.1:7)። ፈቀቅ ስንልም ለትኁታን ጥበብ እንደምትሰጥ ያው መጽሐፍ እንዲህ ይነግረናል። “ትዕቢት ስትመጣ ውርደትም ትከተላለች፤ በትሑት ዘንድ ግን ጥበብ ትገኛለች (ምሳሌ 11:2)።
ሌላውና ንባብ ነው። ንባብ ስንል ደግሞ በተለይም መጽሐፍ ቅዱስን መመርመር ላይ ያተኩራል። እናም ጥበብን የራስ ለማድረግ ሌላው ዘዴ ቃሉን ማጥናት ነው። ለምን ቢሉ ቃሉን ማሰላሰል ከፍተኛ ጥበብን ከማስገኘቱም በላይ ሥራዬ ብሎ ቃሉን በማጥናት የሚሸመተው ጥበብ አስተማማኝ ነው።

No comments:
Post a Comment