በክፍል አንድ ከአንድ እስከአስራስድስት
በክፍል ሁለት ደግሞ ከ17-32 አስፍረናል። እነዚህ ከ33-47 ያሉት ናቸው።
33 ዐውድህን ስትመርጥና ስታዘጋጅ በመንፈስ ቅዱስ ለሚመጣው ትምህርት ሁነኛ ቦታ ስጠው።
34 ስብከቶችህ ከልብ የመነጩ እንጂ የጭንቅላት እውቀት አይሁኑ።
35 ጥልቀት በሌለው ንባብና ጥናት ወይም በሰሚ ሰሚ ሳይሆን የተለማመድከውን ስበክ።
36 ሁሌም መንፈስ ቅዱስ ልብህ ላይ የሚያስቀምጠውን የወቅቱን ቃል አቅርብ። እርሱ የሚያቀብልህን ነጥቦች አጥብቀህ ያዝና በተቻለህ መጠን በቀጥታ ለጉባዔው አድርስ።
37 ሁሌም ልትሰብክ ስትነሣ ከጓዳህ በጸሎት ተሞልተህ መንፈስ ቅዱስ በውስጥህ እየቃተተና በከንፈሮችህም ሊናገር እየፈለገ ሳለ ወደመድረኩ ዝለቅ።
38 አፍህን ስትከፍት ንግግርህ ይፈጥንና እንደጎርፍ ይወርድ ዘንድ አእምሮህ በርዕሰ ጉዳይህ ላይ እንዲነሣሣ አድርግ።
39
ወጥመድን የሚያመጣው ሰውን መፍራት (ምሳ.29:25) በአንተ ላይ አይኑር። እግዚአብሔርን እጅግ ከመፍራትህ የተነሣ ሰዎችን መፍራት እንደማይሆንልህ ሰሚዎችህ ይወቁ።
40 የምትሰብካቸው ሰዎች ስላንተ ያላቸው ዕውቀት በስብከትህ ላይ ተፅዕኖ እንዲያሳድር አትፍቀድ።
41 የቀለብ ጥያቄ “ሰዎች ቢሰሙትም ባይሰሙትም የእግዚአብሔርን እውነት ከማወጅ” አይከልክልህ።
42 በሕዝብህ ዘንድ ያለህን መታመን ስለሚያሳጣህና እንዳይድኑም ስለሚያደርግ አታመንታ። እንደ ክርስቶስ አምባሣደር ተልዕኮህን የመወጣት ቁርጠኝነት ካላዩብህ እንደሚገባ አያከብሩህም።
43 እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊትና ለሰው ሕሊና ሁሉ ራስህን ብቁ አድርገህ ማቅረብን አትርሳ (2 ቆሮ.4:2)።
44 “ያለልክ ገንዘብ ወዳድ” አትሁን።
45 ከንቱ የሆነ አቀራረብን አስወግድ።
46 እውነተኛነትና መንፈሳዊ ጥበብህን እንዲያከብሩ ገፋፋቸው።
47 አፍታም እንኳ ቢሆን የሚሰፈርልህ ቀለብ በጥቂቱም ይሁን ሙሉ በሙሉ ስብከትህን ያስቀይራል ብለው እንዳያስቡ አድርግ።