ሩጫችንን እንጨርስ!
(ቁልፍ አሳቦች በዓለማየሁ ማሞ)
ሰው ሁሉ ይሮጣል። ወደ የትና ለምን ይሮጣል ከተባለ እርሱ ሌላ አነጋጋሪ ጥያቄ ነው።
ከሽልማቱ ውድድሩ ከውድድሩም ልምምዱ ይቀድማል።
ሮጣለሁ የሚል ሰው ሊያደርጋቸው ከሚገቡ ወሳኝ ነገሮች አንዱ ሸክሙን ማራገፍ ነው።
ሕጉን አናክብር። ሯጭነታችን ከሕግ ማምለጫ አገልግሎታችንም ከሥርዓት ማፈንገጫ አይሆነንም።
የክብሩን ውድድር በብቃት ለመጨረስና ለመሸለም የሕጉ እውቀት ያስፈልጋል።
የወደቀውን የሚያነሡ የተፍገመገመውን የሚያበረቱ ቅን ሰዎች በብዛት የሚፈለጉት በሩጫው ሜዳ ላይ ነው።
ሰማያዊው ሩጫ ሲታሰብ በክርስቶስ የመስቀል ሥራ የምናምን ሁሉ የአንድ ቡድን ተሰላፊዎች ነን።
ከአቅማችን በላይ መሮጥ መጀመሪያ ድካምን ቀጥሎም ዝለትን ያመጣብናል። ያኔ ማቋረጥ የሚባል ክፉ አማራጭ
ከፊታችን ይደቀናል።
አማራጩ ወደ ኋላ መመለስ አቋራጩ ማመቻመች አይደለም። መጽናት ነው።
ሩጫውን ጨርሻለሁ ለማለት መጀመሪያ ሳያቋርጡ መሮጥ ያሻል።
ምድራዊው ሽልማት አላፊና ጠፊ ነው። እኛ ግን ለማይጠፋው ሽልማት እንሮጣለን።
የዛሬ ሯጮች እኛ ነን። የምሕረት ደጅ ሳይዘጋ ክፉዎቹ ቀኖችም ሳይመጡ ወደ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም እንሩጥ።
እንጨርስ:: ከመነሻችን ይልቅ መድረሻችን ይቀርባል፤
ከመመለስም ይልቅ መጨረሱ ይቀለናል!
ታላቁ ሩጫ ከሚለው መጽሓፌ