የማዕበል መንገደኞች
የዚህች መጽሓፍ ዓላማ ውኃው በመርከቦችና በውስጡም ባሉ ሰዎች ላይ የሚያደርሰውን እንግልት መተረክ አይደለም። ይልቁንም
እንደ ማዕበል ስለሚያንገላታን ምድራዊ ኑሮ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው። ከምንም ይልቅ የዚህች ጥራዝ ተልዕኮ የማዕበል መንገደኞች መሆናችንን ማስታወስ ነው።
ውስጣዊው ነውጥ ማንነትን ይሞግታል። ሰው ሠራሽና ተፈጥሮአዊ አደጋዎችም ቢሆኑ አናዋጮች
ናቸው። ልክ ማዕበሉ መርከቦችን እንደሚያንገላታቸው ከግራ ወደ ቀኝም እንደሚያላትማቸው እንዲሁ የሰውን ልጅ ያደርጉታል።
ይንጡታል። ያፈናቅሉታል። አንዳንዶቹን እንጂ ሁሉንም ማስወገድ ደግሞ አንችልም። ናዳውን በእርከን መገደቡ ተሳክቶልናል። ዐውሎ
ነፋሱን ግን ለመከልከል የሚያስችል ቴክኖሎጂ አላገኘንም። እናም ነውጡ አብሮን ይኖራል። ለዚህ ነው የማዕበል መንገደኞች መባላችን።
ከውስጥ ገጾች